Search
Close this search box.

Rift Valley Institute

Making local knowledge work

የኃይማኖትና የብሔር ግጭት በሐዋሳ፡ ኃይማኖታዊ ክ ፍፍልና ማኅበረሰባዊ ሰላም

ማጠቃለያ

  • በሰኔ ወር 2010 እና በሐምሌ ወር 2011 በደቡብ ኢትዮጵያ ቀዳሚ የንግድ ማዕከል እና የደቡብ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ሐዋሳ አሰቃቂ ግጭቶች ተከስተዋል። የመጀመሪያው ጥቃት ድንገተኛ ቢመስልም፣ የሁለተኛው ጥቃት በደንብ የታቀደ ይመስል ነበር። ጥቃቱ ኤጄቶ በመባል የሚታወቁት የሲዳማ ወጣቶች ከሲዳማ ፖለቲከኞች ትዕዛዝ ተቀብለው የቀሰቀሱት ጥቃት ነው የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።
  • ግጭቱ ከመከሰቱ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት የሐዋሳ ከተማ ምቹ እና ሰላም የሰፈነባት ከተማ በመሆኗ እንዲሁም፣ በብሄር እና በኃይማኖት ብዝሃነቷ ትታወቅ ነበር። በከተማዋ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች በቁጥር በርካታ ሲሆኑ፣ መጠናቸውም የበዛ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እና አነስተኛ የሙስሊም እና የካቶሊክ እምነት ተከታዮችም አሉ። ከዚህ በተጨማሪም የሲዳማ ባህላዊ እምነት ተከታዮች ቁጥር ላይ ጉልህ እድገት ታይቷል። ይህ በንዲህ እንዳለ በሐዋሳ የተቀሰቀሰው ግጭት በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ከነበሩት ኃይማኖትን መሠረት ካደረጉ ወቅታዊ ግጭቶች በተቃራኒ ከሲዳማ ብሔርተኝነትና የሲዳማ ክልል ምስረታን ዕውን ለማድረግ ከተደረገው የፖለቲካ ትግል ጋር የተገናኘ ነው። ስለዚህም የተመሳሳይ ኀኃይማኖት ተከታዮች፣ በተለይም ፕሮቴስታንቶች በብሔር ልዩነት ላይ ተመሥርተው እርስ በርስ ተጠቃቅተዋል።
  • ያም ሆኖ ግን በርካታ አብያተ ክርስቲያን የብሔር መለያያ መድረኮች በመሆናቸው፣ እንዲሁም አንዳንድ ክርስቲያኖች ግጭቱን በንቃት በመደገፋቸው ኃይማኖት በግጭቶቹ በቅርበት ተሳትፏል። ከዚሁ ጎን ለጎን በርካታ የኃይማኖት አባቶች እና እንደ የሐዋሳ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ያሉ ተቋማት በሰላማዊ መንገድ ተሳታፊዎችን በማግባባት በግጭቶቹ ወቅትም ሆነ በኋላ አስተዋፆ አበርክተዋል።
  • የ2010 እና የ2011 ግጭቶች የሐዋሳ ከተማ የርስ በርስ እና የኃይማኖት ግንኙነቶችን በከፍተኛ ሁኔታ ቀይረዋል። ቀደም ሲል ተደማጭነት የነበራቸው የማኅበረሰቡ መሪዎች በግጭቶቹ ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል ምክንያት ስማቸውን እና ጠቀሜታቸውን አጥተው ነበር። በዚህም ምክንያት አዳዲስ የፕሮቴስታንት መሪዎች በግጭቱ ወቅት እና በኋላ ባደረጉት የሰላም ማስከበር እና የማስታረቅ ሥራ ትኩረት እያገኙ ነው።
  • አሁን ያ ለው ሁ ኔታ በች ግር የ ተሞላ ቢ ሆንም፣ ያሉትን የ ሰላም ግ ንባታ ው ጥኖች በ ጊዜ ሂ ደት በ ተገቢው ውስጣዊ እና ውጫዊ ድጋፍ ማራዘም እና ማስቀጠል ከተቻለ፣ የኃይማኖት ማኅበረሰቦች የግጭት መንስዔ የፖለቲካ መድረኮች ከመሆን የሰላምና እና ልማት አቀላጣፊነት የመቀየር ተስፋን ከፍ ያደርገዋል።

Find the English version of this report here.

  • Recent Publications