Search
Close this search box.

Rift Valley Institute

Making local knowledge work

የጨው ፖለቲካ በአፋር ክልል፡ አግላይ የንግድ ሥርዓትና አንድምታው 

 ማጠቃለያ 

  • በኢትዮጵያ የአፋር ክልል በተለይም የአፍዴራ ሐይቅ ዙሪያ ለኢትዮጵያ ትልቅ የጨው ምንጭ በመሆን 80 በመቶ የሚሆነውን የሀገር ውስጥ የጨው ገበያ ይሸፍናል። በክልሉ ያለውን የጨው ዘርፍ ጨው ማወጣት ከተጀመረበት ከ1990 (እ.ኤ.አ. 1998) አንስቶ አብዛኛው ድርሻ ከአፋር ክልል ከአጎራባች ክልሎች እና ከሀገሪቱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማዕከል በመጡ ‘ደገኞች’ ተይዞ አፋሮች አነስተኛ ሚና ብቻ በመጫወት ላይ ይገኛሉ። 
  • ከ2010 (እ.ኤ.አ. 2018) ጀምሮ የክልሉ አዲስ የፖለቲካ አመራር ልችግሩ መፍትሄ እንድሚያብጀ ቃል ቢገባም፣ የአፋር ክልል በዘርፉ ውስጥ ያለው አነስተኛ ሚና አሁንም እንደቀጠለ ነው። ይህም ጨዋማ መሬቶችን ለአፋር ማኅብረተሰብ ክፍሎች (የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ አርበኞች፣ ድርጅቶች ወዘተ) ማከፋፈልን ያካትታል። 
  • ከሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ጋር ቁርኝት የነበራቸው የጨው ንግድ ድርጅቶች በ2010 በመጣው መንግሥት ሲወሰዱ፣ አዲስ የፖለቲካ ጥቅም ያላቸው ነጋዴዎች የጨው ንግድን ለመቆጣጠር ጥረት አድርገዋል። ከአዲሱ የክልሉ አመራር በስተቀር አሁንም የአፋር ማኅበረሰብ በጨው ምርት ላይ ያለው ሚና ኢምንት ነው። ይህም የትርፍ ኅዳጉን በፍጥነት እየቀነሰው ይገኛል። 
  • በአሁኑ ጊዜ ኤስቪኤስ ሳልት ፕሮዳክሽን ኃ.የተ.የግ.ማ. (ኤስ.ቪ.ኤስ.) እና እህት ኩባንያው ቲቲአር ጨው ማምረቻ የጨው ምርቱን ተቆጣጥርውታል። 
  • ይህም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የጨው ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ካደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የአዮዲይዜሽን ጥረቶች – የተንሰራፋውን የአዮዲን እጥረት ለመቀነስ የተማከለ ፕሮግራም – ላይ ለተከሰቱት ውድቀቶች በከፊል ተጠያቂ ነው። ይሁን እንጂ ፕሮግራሙ ባለማወቅ አፋሮችን ከጨው ዘርፍ አግልሎ በትልልቅ ባለሀብቶች የፖለቲካ ተፅዕኖ በማሳደር የሞኖፖሊ አሰራርን አጠናክሯል። 
  • የጨው ዕሴት ሰንሰለትን ለመቆጣጠር የወጣው የ2015 መመሪያ፣ በተለይ አዲሱ ብርቂቀ ላይ የሚገኘው የጨው ሂደት ሃብቱ በሚገኝበት እና በሚወጣበት ክልል ላይ የሚገድበው አንቀጽ አሁን ያለውን ሞኖፖሊ የበለጠ ሊያጠናክር ይችላል። ይህም ከአፋር ክልል ውጪ የሚሰሩ በደርዘን የሚቆጠሩ የጨው ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን ከስራ ውጪ ሊያደርግ ይችላል። 
  • አሁን ያለው የጨው ዕሴት ሰንሰለት የክልሉን አስተዳደርና የአገር ውስጥ ተጠያቂነትን በማዳከም የጨው ኪራይ ሰብሳቢነት የአፋር ክልል አመራር በሰመራና በአፋር ክልል ያለውን የአገር ውስጥ ምርጫ ከማጠናከር ይልቅ የአዲስ አበባን የፖለቲካና የንግድ ልሂቃንን እንዲያስተናግድ አድርጓል። በክልሉ ያለው የተትረፈረፈ ጨው አካባቢውን የመለወጥ አቅሙ ሊሟላ አልቻለም ሲሉ በምሬት የሚናገሩት የአፋር ክልል ተወላጆች፣ በክልሉ የፖለቲካ መደብ መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ቡድንተኝነትን እና ቅሬታን ፈጥሯል ይላሉ። 
  • የአፍዴራ ጨውን የበለጠ ፍትሐዊ እና አካታች ለማድረግ እንዲሁም ሰላማዊ አስተዳደርን ለማስፈን በዘርፉ የተሰማሩ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን አመለካክት መቀየር ይጠይቃል። ይህም የጨው ረቂቅ ሕ ሞኖፖሊን ለመቆጣጠርና የጨው ዋጋ ተመነን ለማሻሻል በአፋር ክልል ብቻ ሳይሆን በመላ ሀገሪቱ ለጨው አምራቾች፣ አቀነባባሪዎች እና አከፋፋዮች እኩል ዕድሎችን በፉክክር የገበያ ሥርዓት ውስጥ መፍጠር ማስቻል ይኖርበታል። 
  • የአፋር ማኅበረሰብን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጨው ዘርፉ ያለውን የንግድ አቅም አሟጥጦ መጠቀም ያስፈልጋል። ይህም በአጠቃላይ የክልል መሪዎች እና የማዕከላዊ መንግሥትን የፖለቲካ ተቀባይነት መሠረት አድርጎ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ አካታች አጀንዳን ይጠይቃል። 

Find the English version of this report here.

  • Recent Publications