Search
Close this search box.

Rift Valley Institute

Making local knowledge work

የሴቶች ሚና በኢትዮጵያ ክልልላዊ እና አገር አቀፍ የሰላም ሂደቶች

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሴቶች የተለያዩ የፖለቲካ፣ የጸጥታ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ተግዳሮቶች ያጋጥሟቸዋል። በሌሎች አገሮች እንደሚታየው ሁሉ፣ በኢትዮጵያ የሚከሰቱ ግጭቶች ሴቶችን ተመጣጣኝ ላልሆኑ ስቃዮች፥ ጥቃቶችና እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ያጋልጧቸዋል። ይህም የሰላምን አስፈላጊነት የሚያጎላ ሲሆን፣ የሴቶችን እና የልጃገረዶችን ደኅንነት ከማረጋገጥ ባለፈ የሴቶችን መብት ከማክበር ጋር የተያያዘ ነው። ከዚህ ጎን ለጎን የሰላም ሂደቶችን ዘላቂነት እና ህጋዊነት ለማረጋገጥ ትርጉም ያለው የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነው። በአሁኑ ጊዜ ግን ሴቶች በተለያዩ ደረጃዎች ሙሉ ብቃት ያላቸው ሰላም ፈጣሪዎች መሆናቸውን በተደጋጋሚ ቢያሳዩም ለሰላም መስፈን የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ እጅግ በጣም አነስተኛ ነው። ይህ ጽሑፍ የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ሂደቶችን በምሳሌነት በመጠቀም በእነዚህ ሁለት ሂደቶች ውስጥ የሴቶች መካተት እስካሁን በታዩት ውጤቶች ላይ እንዴት ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ያሳያል።

Find the English version of this briefing here.

  • Recent Publications