የኦጋዴን ተፋሰስን ማንጠፍጠፍ፡ የተንጓተተው የሶማሊ ክልል የነዳጅ ሐሰሳና የሥልጣን ፍትጊያ

ማጠቃለያ

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል 350,000 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የኦጋዴን ተፋሰስ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ክምችትን ጨምሮ በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገ ነው። እነዚህ ሀብቶች በአግባቡ እና በፍትሃዊነት ጥቅም ላይ ከዋሉ ለክልሉ እና ለሀገሪቱ አጠቃላይ ልማት አስተዋፅዖ የማድረግ አቅ ምአላቸው። ይሁን እንጂ በፌደራል መንግስት አማካኝነት በሶማሌ ክልል ተጓዳኝ ሀብቶች ለማግኘት የሚደረጉ ጥረቶች በረመዥም ዓመታት የአመጽና ከንብረት የማፈናቀል ታሪክ ጋር የተሳሰሩ ናቸው።

የሶማሌ ክልል ከ2010 (እ.ኤ.አ. ከ2018) መጨረሻ ጀምሮ – ማለትም የቀድሞ የክልሉ አስተዳዳሪ አብዲ መሃሙድ ዑመር (‘አብዲ ኢሌይ’) ከሥልጣን ከተባረሩ በኋላ አንጻራዊ ሰላም ታይቶበታል። በሥልጣን ላይ ባለው መንግሥት ፖለቲካዊ ተሳትፎን እና ኢኮኖሚውን መልሶ ለማደራጀት የተገባው ቃል የሶማሌ ክልል ተወካዮችን ወደ ብልፅግና ፓርቲ ከማዋሃድ ባለፈ ነዳጀና ጋዝን በተመለከተ እስካሁን ሊሟላ አልተቻለም።

በ2014 (እ.ኤ.አ. በ2022 ዓ.ም.) ፖሊ-ጂሲኤል የተሰኘው የቻይና ኩባንያ ከነዳጅ ፍለጋ መባረሩን ተከትሎ በኦጋዴን ተፋሰስ ውስጥ የነዳጅ እና ጋዝ ፍለጋን የማስቀጠል እና የማምረት እቅድን በተመለከተ በፌዴራል መንግሥት የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር ወይም በሶማሌ ክልል አመራሮች ግልፅ የሆነ ፍኖተ ካርታ አልተሰጠም። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ለረጅም ጊዜ የዘለቀው የነዳጅ እና ጋዝ ፍለጋ እስካሁን ድረስ ቁፋሮው እና የውጪ ንግድ እንቅስቃሴው ለሶማሌ ክልል እና ለአጠቃላይ ኢትዮጵያ ገቢ የሚያስገኝ ውጤት አላመጣም።

በተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር ዙሪያ የአካባቢውን ማህበረሰቦችን ለማሳተፍ ከብልፅግና ፓርቲ አስተዳደር የተወሰነ ጥረት ቢደረግም ሰፋ ባለ መልኩ እንደ ቀድሞው ኢሕአዴግ በነዳጅ እና በጋዝ አስተዳደር ላይ ለሚኖረው ሕጋዊነት ውስን የማኅበረሰብ አባላትን የመጥቀም አዝማሚያ እየታየበት ነው።

ከሶማሌ ክልል የተውጣጡ ተቃዋሚዎች እና የዲያስፖራ አባላት በመንግሥት ድጋፍ በሚንቀሳቀሱና ተጠያቂነት በሌላቸው የውጭ የነዳጅ እና ጋዝ አውጭ ኩባንያዎች ላይ እንዲሁም በተያያዥ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ጉሰቁለናዎቸነበተመለከተ ግንዛቤ በማሳደግ ላይ ናቸው። ይህ በሱማሌ ክልላዊ መንግሥት በሲቪል ማኅበረሰብ እንቅስቃሴ ውስጥ ጠቃሚ ዕድገትን የሚያመለክት ቢሆንም፣ በነዳጅና ጋዝ ፍለጋ ውስጥ የሚከስተውን ቀጣይነት ያለው ውዝግብ ያሳያል። በሶማሌ ክልል አመራር አካላት ሁሉን አቀፍ ውይይት በበቂ ሁኔታ ካልተስተናገደ ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የተጀመረውን ተስፋ ሰጪ የሰላም ሂደትም ሊያደናቅፍ ይችላል።

እስካሁን ድረስ በኦጋዴን ተፋሰስ የታየ የአካባቢ እና የሰው ጤና ሥጋት ባይኖርም፥ ራሱን የቻለ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አልተካሄደም። ፖሊ-ጂሲኤል እና ሌሎች ኩባንያዎች በተገለለ መልኩ ቢሠሩም፣ ለአካባቢው ሕዝብ በቂ ጥቅሞችነ አልሰጡም። በመሆኑም በፌዴራል መንግሥት እና በፖሊ-ጂሲኤል መካከል የተፈረሙት ስምምነቶች ነባር የማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ማግለል ተዋረዶችን አጠናክረው ቀጥለዋል፣ ይህም ሥራ እና ኮንትራቶች ከኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማዕከል በሚመጡት ‘ደገኞች’ እንዲያዝ አድርጓል።

የአዲስ አበባ ማዕከላዊ መንግሥት ቅጥያ ተብሎ የሚተቸው የሶማሌ ክልል፣ ይህ ከለልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የጀመረው ግንኙንትና የሳበው ትኩረት ለክልሉ ሕዝብ ተጨባጭ ጥቅሞች እንደሚሰጥ ማረጋገጥ አለበት። በተጨማሪም የሃይድሮካርቦን ስትራቴጂ ልማቱ ሰፊ ምክክር እና ማኅበረሰብን ያማከለ አካሄድን ማካተት አለበት። በ2011 (እ.ኤ.አ. በ 2019) የተወሰነዉ የገቢ መጋራት ቀመር ግልፅነት የጎደለው ነው ተብሎ ቢተችም፣ የኦጋዴን ተፋሰስ የክልል ተወካዮች ነዳጅቨእና ጋዝን እንደ ፖለቲካ ካፒታል በመጠቀም አገራዊ አቋማቸውን የሚያጎለብቱበት እንዲሁም የሚፈለገውን ኢኮኖሚያዊ ፍትህ ለማስፈን የሚችሉበት ዕድል ፈጥሯል።

Find the English report here and the Somali summary here.

  • Recent Publications

    የድሬ ዳዋ ከተማ መልከ ብዙ ውዝግቦት

    ከኢትዮጵያ ከተሞች በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ የሆነችው ድሬ ዳዋ ከተማ፣ በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል የብሔረሰቦች፣ የቋንቋ እና የኃይማኖት ብዝኃነት የሚገለጥባት ማዕከል መሆኗ ይታወቃል። ነገር ግን በ2010 የተደረገውን

    MORE »