ኃይማኖታዊ ዋልተኝነት በኢትዮጵያ፡ የከተማ ግጭቶች እና የሰላም ዕድሎች

ማጠቃለያ

• ይህ ዘገባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአዲስ አበባ ውጪ በኢትዮጵያ በተከሰቱት የማኅበረሰብ ግጭቶች ውስጥ
የኃይማኖት ሚናን ያጠናል። በመዲናይቱ ያለውን አለመግባባቶች እና አመለካከቶች ሙሉ በሙሉ ችላ
ባይልም በኢትዮጵያ ውስጥ ከአራት የክልል ከተሞች ማለትም ከድሬዳዋ፣ ከጎንደር፣ ከሐዋሳ እና
ከጅማ የተገኙ መረጃዎችን በማሰባሰብ ስለ ኃይማኖት እና ግጭቶች የተሟላ እና ሁለገብ ገጽታ ለመሳል
ይጥራል። ዘገባው በእነዚህ ከተሞች ውስጥ በተካሄዱ ዋና ጥናቶች ላይ የተመሰረተ ነው። ከእነዚህም
ውስጥ አብዛኞቹ አስቀድሞ ታትመዋል።

• ዘገባው እነዚህን የተለያዩ ቦታዎች በማነፃፀር፥ ኃይማኖት እና ብሔር ግጭትን ከመፍጠር ጋር እንዴት
እንደሚገናኙ፣ የተለያዩ ማበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ምን ሚና እንደሚጫወቱ፣ እንዲሁም
በኃይማኖቶች መካከል ያሉ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች ምን ያህል እንደሚጨምሩ ያጠናል። በተጨማሪም
ዘገባው ግጭት አፈታት እና መከላከል ላይ በአካባቢ የኃይማኖት ምክር ቤቶች፣ በኃይማኖት እና
በፖለቲካ አመራር እና በግል ግንኙነቶች አማካይነት ኃይማኖቶች የሚያበረክቱት አስተዋፅዖ ላይ ወሳኝ
ውይይት ያደርጋል።

• ይህ ዘገባ የተጠኑ ግጭቶችን በተመለከተ መሠረታዊ እውነታዎችን እና መረጃዎችን ከመፈለግ ባለፈ
የሚመለከት ነው። ምንም እንኳን እነዚህ አስፈላጊ ቢሆኑም፣ ጥናቱ በተለይም ኦፊሴላዊ ምርምሮች
በሌሉበት ወይም ተዓማኒነት እንደሌላቸው በሚታወቅበት ጊዜ፣ የሰዎች ፍራቻ፣ ተስፋ እና ድርጊት
የሚወሰነው እውነታ ነው ብለው በሚያምኑበት ጉዳይ ላይ እንደሆነ ይገነዘባል። ለዚህም የዘገባው
ዋና ትኩረት በተለያዩ የጥናት ቦታዎች ላይ የተለያዩና ብዙውን ጊዜ የሚቃረኑ አመለካከቶችን እና
አስተያየቶችን በመቅረጽ የወቅቱን የኃይማኖት እና የግጭት አመለካከቶችን ለመንደፍ ነው።

• በዚህ ጥናት ውስጥ ከተገኙት ግንዛቤዎች ጋር በማዋሃድ ዘገባው ኃይማኖትን እንደተለየ ማኅበራዊ
ጉዳይ ሳይሆን እንደ አንድ ተጨባጭ የልምድ እና የእምነት ስብስብ በማስቀመጥ ከታሪካዊ ትረካዎች፣
ከብሔር ማንነቶች፣ ከዘይቤዎች፣ ከሥራ እና ከሌሎች ማኅበራዊ መመዘኛዎች ሙሉ በሙሉ ሊነጣጠል
እንደማይችል ገልጿል። በተጠኑት ግጭቶች ሁሉ፣ ኃይማኖቶቸ በአካባቢው ማኅበረሰቦች ላይ ከሚደርሱት
ሌሎች ጫናዎች ጋር በጥምረት በመሥራት በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ግጭትን ለመቀስቀስ ውሳኝ
ማስተላለፊያ እና ማነቃቂያ ሆንወ ያገለግላሉ።

• ይህም ኃይማኖቶችን በሰላም ግንባታ ሥራቸው ለማሳተፍ ለሚፈልጉ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ
ላልሆኑ ኤጀንሲዎች ጠቃሚ አንድምታ አለው። ‘አክራሪ እምነቶች’ ከ ‘ሰላማዊ ኃይማኖት’ ከሚለው
አቅላይ የልየታ አረዳድን ከማስረጠፅ ይልቅ ኃይማኖቶች በግጭት ውስጥ እንዴት እንደሚንቀሳቀሱ
ወይም እንዴት ለሰላም መድረክ አስተዋፅዖ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ዐውዳዊና ዘርፈ-ብዙ ግንዛቤን
ለማስፈን ተጨማሪ ሥራ መሠራት አለበት። ይህ ማለት በኢትዮጵያ የምርምር አቅም ላይ መዋዕለ ነዋይ
ማፍሰስ እና ከሀገር ውስጥ ተነሳሽነት ጋር ተቀራርቦ መሥራት ማለት ነው።

Find the English version of this report here.

  • Recent Publications

    አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ የክላስተር አደረጃጀትና የሀብት ክፍፍል ተግዳሮቶች፡ የዘይሴ-ጋሞ እና ቀቤና-ጉራጌ ድንበርአካባቢ ግጭቶች

    ይህ ሪፖርት በደቡብ ኢትዮጵያ ከ2010 ጀምሮ የተተገበረውን የአስተዳደር ክላስተር መልሶ ማዋቀር ተከትሎ፣ በዘይሴ እና በጋሞ እንዲሁም በቀቤና እና በጉራጌ ብሔረሰቦች መካከል በተከሰቱ ውጥረቶች ላይ ያተኩራል።

    MORE »