በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልል ድንበር አካባቢ የሚገኙ አከራካሪ ቦታዎች ላይ አስተዳደራዊ ቁጥጥርን ለማጠናከር በሚደረገው ፉክክር የሚነሱ ግጭቶች የተዳፈኑ ቢመስሉም ጨርሰው አልጠፉም። ይህ በምስራቅ አፍሪካ ረጅሙ የሀገር ውስጥ የክልሎች ወሰን ሲሆን፥ አካባቢው ከ2009–2011 ግጭት እና የአገር ውስጥ መፈናቀልን ያስከተለም ነበር።
የኢትዮጵያ የሰላም ምርምር ተቋም
ይህ ሪፖርት ለኢትዮጵያ የሰላም ምርምር ተቋም የተጻፈ ሲሆን፥ የድንበር ውዝግቦችን የተመለከቱ ጭብጦች የተዳሰሱበት የዕውቀት ለሰላም (Knowledge for Peace) ምርምሮች አካል ነው። የሰላም ምርምር ተቋም ገለልተኛ የሆነ ወቅታዊ የሰላምና የግጭት ትንታኔዎችን ከኢትዮጵያዊ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች በማቀናጀት በአገሪቱ ግጭት አገናዛቢ የሆነ የፖሊሲና ፕሮግራም ቀረጻ እንዲኖር ያግዛል። ተቋሙ በሪፍት ቫሊ ኢንስቲትዩት (አር ቪ አይ) የሚተዳደር ሲሆን፥ በእንግሊዝ መንግሥት ድጋፍ ይደረግለታል።
Please find the full report in English here.