ከ2010 ወዲህ ያለው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር በጋራ ትውስታዎች የተሰናሰሉ የታሪክ አተረጓጎሞች የፖለቲካ ወገንተንነትን እንደሚቀርፁ የሚያሳይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን እንደመጡ የታላቁ ትውፊት ትርክቶችን (great tradition narratives) ማቀንቀናቸው የርሳቸው ድጋፍ ማዕከል ከሆነውና ይህንን ትርክት ከሚገዳደረው የኦሮሞ ማኅበረሰብ የታሪክ አረዳድ ጋር የሚጋጭ ነበር። በልሒቃን መካከል ከሚታየው የፖለቲካ ተፎካካሪነት ጋር ሲሰናሰል ደግሞ፥ ይህ አለመጣጣም በታሪክ አረዳድና አተረጓጎም ላይ ለሚታየው ከፍተኛ ውዝግብ ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነበር።
የኢትዮጵያ የሰላም ምርምር ተቋም
ይህ ሪፖርት ለኢትዮጵያ የሰላም ምርምር ተቋም የተጻፈ ሲሆን፥ ውዝግብ የሚታይባቸው የከተማ ስፍራዎችን የተመለከቱ ጭብጦች የተዳሰሱበት የዕውቀት ለሰላም (Knowledge for Peace) ምርምሮች አካል ነው። የሰላም ምርምር ተቋም ገለልተኛ የሆነ ወቅታዊ የሰላምና የግጭት ትንታኔዎችን ከኢትዮጵያዊ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች በማቀናጀት በአገሪቱ ግጭት አገናዛቢ የሆነ የፖሊሲና ፕሮግራም ቀረጻ እንዲኖር ያግዛል። ተቋሙ በሪፍት ቫሊ ኢንስቲትዩት (አር ቪ አይ) የሚተዳደር ሲሆን፥ በእንግሊዝ መንግሥት ድጋፍ ይደረግለታል።
Please find the full report in English here.