በኢትዮጵያ ከተሞች የሚታዩ ውዝግቦችን ማጥናት፣ ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ የከተማ ማዕከላት የሚስተዋሉ ጉልህ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦች ምን ዓይነት መልክ እንዳላቸው ለመገንዘብ ይረዳል። በዚህ ረገድ በቅርቡ የተመሠረተው የሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው የቀድሞ የደቡብ ክልል ዋና ከተማ ሐዋሳ ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ጎልተው የታዩ የተለያዩ ውዝግቦች ከክልል በታች ባሉ መዋቅሮች፥ በክልል እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ካስከተሏቸው ለውጦች አኳያ፥ ይህ ጥናት በሐዋሳ መደረጉ ምክንያታዊ ነው። ይህ ጥናት የውዝግቦቹ ተዋናዮች እና ሥፍራዎች በመለየት የውዝግቦቹን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ማስረዳት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ይህ ሪፖርት ለኢትዮጵያ የሰላም ምርምር ተቋም የተጻፈ ሲሆን፥ ውዝግብ የሚታይባቸው የከተማ ስፍራዎችን የተመለከቱ ጭብጦች የተዳሰሱበት የዕውቀት ለሰላም (Knowledge for Peace) ምርምሮች አካል ነው። የሰላም ምርምር ተቋም ገለልተኛ የሆነ ወቅታዊ የሰላምና የግጭት ትንታኔዎችን ከኢትዮጵያዊ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች በማቀናጀት በአገሪቱ ግጭት አገናዛቢ የሆነ የፖሊሲና ፕሮግራም ቀረጻ እንዲኖር ያግዛል። ተቋሙ በሪፍት ቫሊ ኢንስቲትዩት (አር ቪ አይ) የሚተዳደር ሲሆን፥ በእንግሊዝ መንግሥት ድጋፍ ይደረግለታል።
Please find the full report in English here.