ይህ ሪፖርት በደቡብ ኢትዮጵያ ከ2010 ጀምሮ የተተገበረውን የአስተዳደር ክላስተር መልሶ ማዋቀር ተከትሎ፣ በዘይሴ እና በጋሞ እንዲሁም በቀቤና እና በጉራጌ ብሔረሰቦች መካከል በተከሰቱ ውጥረቶች ላይ ያተኩራል። ከ2010 ጀምሮ ከድንበር ይገባኛል እና ራስን በራስ ከማስተዳደር ጥያቄዎች ጋር ተያይዘው የሚነሱ ግጭቶች በኢትዮጵያ እየጨመሩ መጥተዋል። ሆኖም የሚከሰቱ የሰላምና የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት፤ ብልጽግና ፓርቲ በቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ውስጥ የክልል እና የአካባቢ አስተዳደሮችን በአዲስ መልክ አዋቅሯል።
Read the English version here.