ይህ ጽሑፍ አዲስ በተቋቋመው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በሀዲያ ዞን በምትገኘው ሆሳዕና ከተማ ለሀብት ባለቤትነት እና ቁጥጥር የሚደረግ ውዝግብ ላይ የተደረገ ጥናት ሪፖርት ነው።
ጥናቱ የከተማዋን መስፋፋት ተከትሎ በቀድሞ በተወሰኑ ቡድኖች ተይዞ የነበረው የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኃይል ተገለው በነበሩ የአካባቢው ተውላጆች መተካቱን በማሳየት፣ የሀዲያ ተወላጆች ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያደርጉት ፍልሰት በእነዚህ አዳዲስ ለውጦች ላይ ያሳድርውን ሚና የሚያስስ ነው።
ይህ ሪፖርት ለኢትዮጵያ የሰላም ምርምር ተቋም የተጻፈ ሲሆን፥ ውዝግብ የሚታይባቸው የከተማ ስፍራዎችን የተመለከቱ ጭብጦች የተዳሰሱበት የዕውቀት ለሰላም (Knowledge for Peace) ምርምሮች አካል ነው። የሰላም ምርምር ተቋም ገለልተኛ የሆነ ወቅታዊ የሰላምና የግጭት ትንታኔዎችን ከኢትዮጵያዊ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች በማቀናጀት በአገሪቱ ግጭት አገናዛቢ የሆነ የፖሊሲና ፕሮግራም ቀረጻ እንዲኖር ያግዛል። ተቋሙ በሪፍት ቫሊ ኢንስቲትዩት (አር ቪ አይ) የሚተዳደር ሲሆን፥ በእንግሊዝ መንግሥት ድጋፍ ይደረግለታል።
Please find the full report in English here.