Search
Close this search box.

Rift Valley Institute

Making local knowledge work

ጠረፋማ አካባቢዎችን ማበልጸግ? የመዋዕለ ንዋይና የማዕድን ቁፋሮ ፖለቲካ በድካረ 2010 ኢትዮጵያ

ማጠቃለያ

  • በ2012 (እ.ኤ.አ. በ2019) የብልጽግና ፓርቲ ምስረታን ለስከትሎ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመራው መንግሥት የማዕከላዊ መንግሥትንና እና ‘የጠረፍ አካባቢዎችን’ ክልላዊ መንግሥታት ግንኙነት ለማስተካከል ወጠነ። ይህም የመዋለ ንዋይና የገቢ ክፍፍል አስተዳደር ማሻሻያዎችን ያካተተ ሲሆን፤ በተፈጥሮ ሀብቶች የበለፀጉ ግን በፖለቲካ የተገለሉ ክልሎች ፍትሕዊ ‘ብልፅግናን’ እንዲያገኙ ያለመ ነበር። 

  • የብልጽግና ፓርቲ አመራር የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ይከተለው ከነበረው መንግሥት መራሹ ልማታዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመውጣትና የገበያ ነፃነትን በመተግበር፤ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን (ለምሳሌ፣ ስኳር ማምረቻዎችን) ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር፣ በማዕድን ቁፋሮ ዘርፍ (ማለትም በወርቅ፣ በነዳጅ/ዘይት) ኢንቨስትመንቶችን ለማሳደግ እንዲሁም የአፈፃፀም ድክመት ያላቸውን ዘርፎች (ለምሳሌ ጨው፣ ስኳር) ምርታማነት ለማሻሻል ቃል ገብቷል። 

  • የማዕድን (የጨው/ወርቅ) ቁፋሮ ሥራ ዕድሎችን ለወጣቶች ወይም ለሰፊው የኅብረተሰብ ክፍል ማስተላለፍ፣ እንዲሁም ከሚገኘው ገቢ ከፍተኛውን ድርሻ በክልሎች ለማስቀረት ቃል መግባትን ጨምሮ የታቀዱት የመልሶ ክፍፍል ማሻሻያዎች፣ በአብዛኛው ፖለቲካዊ ተነሳሽነት ያላቸው ሲሆኑ የተወሰኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን አፍ ለማስያዝና ለመንግሥት ታማኝ የሆኑ የክልል ባለህብቶችን ለመፍጠር/ ለመያዝ ያለሙ ነበሩ። 

  • በብልጽግና ፓርቲ የሚደገፉና በዋናነት ከኦሮሚያ እና ከአማራ ክልል የተውጣጡ ባለሀብቶች ከዚህ ቀደም በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ተባባሪዎች ወይም በመንግሥት የተያዙ ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚ ዘርፎችን (ለምሳሌ ወርቅ፣ ስኳር እና ጨው) ይዘዋል። ይህም የፖለቲካ ማዕከሉ የክልል አሊያም የብሔር ጥምረቱን በቀየረ ቁጥር ያሉትን የማዕድን ቁፋሮ ሀብቶች ለመቆጣጠር ያለመ ፉክክርን ቀስቅሷል። 

  • በብልጽግና ፓርቲ አመራር ዘመን የሚስተዋሉ አንዳንድ የኢኮኖሚ ችግሮች ስትራቴጂያዊ የማዕድን ዘርፎችን ማስተጓጎላቸውን ቀጥለዋል። ዋና ዋና ሀብቶችን (ለምሳሌ ጨውና ስኳር) በሞኖፖል መያዝ፣ የማኅበረሰብ ምክክር እና የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አለማካሄድ፣ ዉጤታማ ያልሆኑ ፕሮጀክቶችን መሰረዝ (ለምሳሌ ዘይት/ጋዝ፣ ወርቅ) እንዲሁም በአስተዳደር ጉድለትና በምርታማነት ዕጦት ያልተሟሉ የፕራይቬታይዜሽን ሥራዎች (ሀብትን ከመንግሥት ወደ ግል ይዞታ ማዘዋወር) ከችግሮቹ መካከል ይጠቀሳሉ። እነዚህ ሁኔታዎች የፓርቲውን የመጀመሪያ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ በማጓተት ወደ መጪው ሁለተኛ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ተላልፈወዋል። 

  • ከማዕድን ቁፋሮ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ግጭቶች እና ሁከቶች የተለመዱ ናቸው። እነዚህ ግጭቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚከሰቱትን የድንበር እና የግዛት ግጭቶች፣ የብሔር ተኮር ጥቃቶች እንዲሁም በመንግሥት የሚመሩ ትጥቅ የማስፈታት እና የመልሶ ማቋቋም ዘመቻዎች ምክንያትነትን ያካተቱ ናቸው። 

  • መንግሥት አምራች የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ለሰላም ግንባታ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክቱ ይናገራል። ብዙ ጊዜ ግን እንደዚህ ያሉ ፕሮጀክቶች ለሀብት ክፍፍል ውዝግቦችና ለግጭት ተጋላጭ ናቸው። ይህም በተለይ በፕሮጀክቶች ምስረታ እና አሠራር ላይ የማኅበረሰብ ምክክርን ካልተከተለ ወይም የታጠቁ ፀረ-አሸባሪዎች እና የተደራጁ ወጣቶች ፕሮጀክቶቹ የፌደራል መንግሥትን ወይም የክልል ባሀብቶችን ብቻ የሚጠቅሙ ከመሰላቸው የሚፈጠር ይሆናል። 

  • የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን የመሀል-ዳር ፖለቲካ ለማስተካከል ቃል ቢገባም፣ በክልሎች እና በፖለቲካ ማዕከሉ መካከል ያለው የኃይል ሚዛን አልተቀየረም። ይሁን እንጂ፤ ምንም እንኳን የተለያዩ ጥምረት አጋርነት መፍጠሪያ መንገዶች ቢሆኑም አዳዲስ ፖሊሲዎችን ማውጣት፣ የፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ስራዎችን መስራት፣ የፖለቲካ ሃይሉን ማዕከላዊ ማድረግ እንዲሁም አንዳንድ (የብሔር ትስስር ያላቸው) ባለሃቶችን ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ በፓርቲው ሥር ቀጥሏል። 

Find the english version of the report here.

  • Recent Publications