Search
Close this search box.

የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና የበረታው ቅሬታ : በኦሮሚያ ጉጂ ዞን በሚድሮክ እና በጎዱ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮዎች ዙሪያ ያለው ውዝግብና ሥጋት

ማጠቃለያ

በአገር አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ለውጥ ቢደረግም በኦሮሚያ ክልል በሚገኙት ሁለቱ የጉጂ ዞኖች (ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ) የማዕድን ቁፋሮ ሥራ የአካባቢውን ማኅበረሰቦች ማግለሉን ቀጥሏል። ይህ እውነታ በተለይ በሳውዑዲ ቢሊየነር ሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ባለቤትነት በሚተዳደረው የሚድሮክ የማዕድን እና የነዳጅ ኩባንያ ላይ ይስተዋላል።

በብልጽግና ፓርቲ ወቅት የተቋቋሙ እንደ ጎዱ አጠቃላይ ትሬዲንግ አ.ማ. (GODU) ያሉ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በ2010 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. በ2018) ሚድሮክ በክልሉ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ውዝግብ ለማርገብ ወጣቶች እና የአካባቢው የንግድ ልሂቃን እንዲሳተፉ አድርጓል።

በ2010 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. በ2018) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የብልጽግና ፓርቲ ወደ ሥልጣን መምጣት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ አዳዲስ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተዋናዮችን አፍርቷል። ይህም በኦሮሚያ ክልል ወርቅ ለማውጣት የሚሰጠውን ፈቃድ ቁጥር ከፍ እንዲል ምክንያት ከመሆነ ባለፈ፣ በተለይ በጉጂ ዞኖች አዲስ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ሽሚያ እንዲፈጠር አድርጓል።

ይሁን እንጂ በአንዳንድ አዲስ የማዕድን ፕሮጀክቶች ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ታይቷል። እ.ኤ.አ. ከ2018 ጀምሮ መንግሥት አስራሩን ተቃዋሚዎቸን ከመጠምዘዝ፣ በግዳጅ መሬት መንጠቅን ጨምሮ ወደ ጉልበትና የጭቆና እርምጃዎች ቀይሯል ።

የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ቁፋሮ በሰዎች እና በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ተከትሎ በተፈጠረው ተቃውሞ መንግሥት በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም. የኩባንያውን ፈቃድ አግዶ ነበር። የተቃውሞው ዋና ዋና መንስኤዎች ሳይታረሙ የማዕድን ቁፋሮው በመጋቢት ወር 2013 ዓ.ም. እንደገና እንዲከፈት ተፈቅዶለታል። ይልቁንም የሚድሮክ ቦታ የሆነውን የኦኮቴ ማዕድን ወደ ጎዱ (GODU) በማዛወር በአካባቢው ልሂቃንን እና ነጋዴዎች የሚድሮከነ ፈቃድ መታድሰ እንዳይቃወሙ ለማድርግ ተሞክሯል።

ግልጽ የሆነ የማኅበራዊና አካባቢያዊ ተፅዕኖ ግምገማ ባለመኖሩ እና የማዕድን ቁፋሮ ሥራው በአንጻራዊነት በቅርብ ጊዜ በመጀመሩ እንደ ጎዱ (GODU) ያሉ አዲስ የተቋቋሙ ኩባንያዎች ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ተፅዕኖዎቻቸው ገና ግልፅ አይደሉም። ነገር ግን የአካባቢው ማኅበረሰብ በሚድሮክ ላይ ያለው ቅሬታ በተጨባጭ የሚታይ ነው።

ይህ ለኢትዮጵያ የሰላም ምርምር ተቋም የተጻፈው ‘የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና የበረታው ቅሬታ፡ በጉጂ ኦሮምያ በሚድሮክ እና በጎዱ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮዎች ዙሪያ ያለው ውዝግብና ሥጋት’ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ሪፖርት ማጠቃለያ ትርጉም ነው። የሰላም ምርምር ተቋም በግጭት ምክንያቶችና አባባሾች እንዲሁመ ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በቂ መረጃ የሚሰጥ ዕውቀት በማመንጨት በኢትዮጵያ ልሰላም ግንባታ ፕሮግራሞች ድጋፍ የሚያደርግ ተቋም ነው። ተቋሙ የሚተዳደረው በስምጥ ሸለቆ የጥናተ ተቋም ሲሆን፣ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት በእንግሊዝ መንግሥት ነው።

Find the English version of this publication here

  • Recent Publications