Search
Close this search box.

Rift Valley Institute

Making local knowledge work

ኃይማኖት እና ግጭቶች በድሬ ዳዋ፡ በይነ ማኅበራዊ ውጥረቶችና የሰላም አማራጮች

ማጠቃለያ

• ድሬ ዳዋ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ስትሆን በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል – በኦሮሚያ እና በሶማሊያ ክልል አዋሳኝ ድንበር ላይ የምትገኝ የብዝሃ-ብሔር እና የኃይማኖቶች የኢኮኖሚ ማዕከል ነች። ምንም እንኳን የከተማዋ ታሪካዊ ሥርዓት በኃይማኖቶች እና በብሔሮች መካከል ባለ ወዳጅነትና መተሳሰብ የሚታወቅ ቢሆንም ድሬ ዳዋ ከ2010 ጀምሮ በተከታታይ በተከሰቱ የማኅበረሰባዊ ግጭቶች ስትታመስ ቆይታለች።


• ቀደም ብለው በከተማዋ የተከሰቱት የመጀመሪያ ዙር ግጭቶች ሙሉ በሙሉ ብሔር ተኮር ግጭቶች ናቸው ሊባሉ ቢችሉም፣ ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች ኃይማኖታዊ ማንነት የግጭቱ አካል እንዲሆን አድርገዋል። በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ኃይማኖታዊ ግጭቶች እና በወጣቱ መካከል እየጨመረ የመጣው የኃይማኖት ውጥረት በኃይማኖቶች መካከል ለሚከሰት ግጭት አስተዋፅዖ አበርክተዋል።


• ይህም ሆኖ፣ የግጭቶቹ ዋነኛ መንስኤ ፖልቲካዊ ይመስላል። የማዕከላዊው ብሔር ተኮር ውዝግብ ከበይነ ሙስሊም (ኦሮሞ እና ሶማሌ) ፉክክር ወደ ክርስቲያን-ሙስሊም (አማራ እና ኦሮሞ/ሶማሌ) ፉክክር ሲቀየር ኃይማኖታዊ ገጽታን አግኝቷል። የእነዚህ ውዝግቦች አካባቢያዊ ባህርይ እንዳለ ሆኖ፣ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ሙስሊሞች በብዛት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች የሚያደርጉዋቸው የጥምቀት ክብረ በዓል ሰልፎች ዋነኛ የግጭት መነሻዎች ሲሆኑ የታያል።

• በኃይማኖቶች መካከል የሚነሱ ግጭቶች እና አክራሪነት እየተበራከቱ ነው ለሚለው አጠቃላይ አመለካከት ማስረገጫ የሚሆን ማስረጃ ባይኖርም፣ በድሬዳዋ ከተማ ግን የየትኛውንም ኃይማኖት የመመሥረት እና የመስፋፋት መብትን የሚነፍግ አንድም ተሳታፊ አልነበረም። በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተከሰቱት ግጭቶች በኃይማኖቶች መካከል ያለውን የሰላም ተስፋ ከሥር መሠረቱ አላስቀየሩም የሚል ሰፊ አስተያየት አለ።


• ይህ ለሰላም ግንባታ ሥራ ትልቅ ዕድል ይሰጣል። የኃይማኖት መሪዎች ለፖለቲካ ወይም ለግል ጥቅማቸው እየሠሩ ነው የሚሉ አንዳንድ ትችቶች ቢሰነዘሩም፣ የኃይማኖት ተዋናዮች በብሔር እና በኃይማኖቶች መካከል ያለውን አለመግባባት በማረጋጋት ረገድ ትልቅ ሚና አላቸው። ምንም እንኳን ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የበለጠ ውክልና እንዲኖርው ጥራት እያደረገና ይክርክር መድረክ ቢሆንም፣ እንደ የኃይማኖት ተቋማት የጋራ ጉባኤ ባሉ ተቋሞች የሚደረጉ የኃይማኖት ውይይቶች በማኅበረሰቡ መካከል ሰላምን የመገንባት አቅም አላቸው።


• በአጠቃላይ የብሔር እና የኃይማኖት ፖለቲካ በተለያዩ ሁኔታዎች ተፅዕኖ የሚደርስባችው ናቸው። እነዚህም የኢኮኖሚ ጫና፣ የወጣቶች ሥራ አጥነት፣ የመሬት እና ፉክክር ናቸው። ይህ ከቀጥታ ውይይት እና ከሰላም ግንባታ ባለፈ ለአስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ትልቅ ዕድል ይሰጣል። ስለዚህ ተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን መፍጠር፣ ለመሬት ድልድል ግልጽ አሠራርን መዘርጋት እና በእያንዳንዱ የከተማዋ ዳርቻዎች ላይ የብሔር እና የኃይማኖት ብዝሃነትን የሚያበረታታ የዞን ክፍፍል እቅዶች ማውጣት ተጨማሪ ግጭቶችን ለመከላከል ትልቅ ሚና ይኖረዋል።

ይህ ለኢትዮጵያ የሰላም ምርምር ተቋም የተጻፈው ‘የወርቅ ማዕድን ቁፋሮና የበረታው ቅሬታ፡ በጉጂ ኦሮምያ በሚድሮክ እና በጎዱ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮዎች ዙሪያ ያለው ውዝግብና ሥጋት’ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ሪፖርት ማጠቃለያ ትርጉም ነው። የሰላም ምርምር ተቋም በግጭት ምክንያቶችና አባባሾች እንዲሁመ ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በቂ መረጃ የሚሰጥ ዕውቀት በማመንጨት በኢትዮጵያ ልሰላም ግንባታ ፕሮግራሞች ድጋፍ የሚያደርግ ተቋም ነው። ተቋሙ የሚተዳደረው በስምጥ ሸለቆ የጥናተ ተቋም ሲሆን፣ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት በእንግሊዝ መንግሥት ነው።

Find the English version of this report here.

  • Recent Publications