Search
Close this search box.

ኃይማኖት፣ ግጭት እና ማኅበራዊ ትስስር፡ ልምዶች ከጅማ ከተማ

ማጠቃለያ

  • ጅማ ዙሪያዋን በእስልምና እምነት ተከታዮች የተከበበች ብትሆንም፤ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሰፊ የማኅበረሰብ ስብጥር ያላቸው ነዋሪዎች ከሚገኙባቸው ከተሞች አንዷ ናት። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መፍረስን ተከትሎ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ኃይማኖትን ብሔር ተኮር አደገኛ ግጭቶች ሲከሰቱ መሰል ግጭቶች ግን በጅማ አልታዩም። ይሁን እንጂ፣ በ1998 እና በ2003 በጅማ ዞን በበሻሻና በአሰንዳቦ አካባቢ በሙስሊም እና በክርስቲያን (ማለትም ኦርቶዶክስና ፕሮቴስታንትን ጨምሮ) እምነት ተከታዮች መካከል ከፍተኛ ግጭት ተከስቶ ነበር።
  • በበሻሻ እ ና በአሰንዳቦ የተከሰቱት ግ ጭቶች በተለያዩ ኃይማኖቶች መካከል የነበረውን ተቻችሎ የመኖር ልማድን እንዳናጉ ይታመናል። በመሬት ባለቤትነት ላይ ያሉ አለመግባባቶች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ዝንባሌዎች እና ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚበረታውን አክራሪነት ጨምሮ፤ ለረጅም ጊዜ የቆዩና ያልተፈቱ ጉዳዮች ተደማምረው አዳዲስ ውጥረቶች በተመሳሳይ መልኩ እንዲታዩ አድርጓል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከ2003 ጀምሮ በከተማዋ እና በአቅራቢያዋ ባሉ አካባቢዎች በኃይማኖት መካከል ምንም አይነት የገዘፈ ግጭት ባያጋጥምም፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ግጭት ዳግም ሊነሳ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።
  • እንደዚህ ዓይነት ስጋት በአንዳንድ አካባቢዎች ጠንካራ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃ ቢያስወስድም፣ በጅማ ግን ሁሉን አቀፍ ውይይት ለማካሄድ እና ሰላሙን ለማስቀጠል በቂ ሥራዎች አልተሰሩም። አንዳንድ የኃይማኖት አባቶች በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ቢሳተፉም ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ባለማግኘታቸው ብዙ ለውጥ አልመጣም። ከጅማ ኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አጥጋቢ ምላሽ ባለመኖሩም በውይይቶት መዋቅራዊ ጉዳዮችን ሳይፈታ የፖለቲካ ዓላማን ብቻ ያከናውናል የሚል አስተሳሰብ እንዲጎላ አድርጓል።
  • ይሁን እንጂ፣ በተለያዩ ኃይማኖቶች ተከታዮች መካከል ያለው ግለሰባዊ ግንኙነት ውስጥ የሚታየው ትስስር እና መተሳሰብ ብርቱ ይመስላል። በከተማዋ በተለያዩ የኃይማኖት ተከታዮች መካከል በሚደረጉ ጋብቻዎች ላይ አልፎ አልፎ ከሚታዩ ጥርጣሬዎች በስተቀር ኃይማኖታዊ መቻቻል አለ። ጥናቱ በቤተሰብ ግንኙነት፣ በጓደኝነት ወይም በሥራ ቦታ ባሉ የተለያዩ የሕይወት ዘርፎች ውስጥ ከኃይማኖት ልዩነቶች የሚሻገር መከባበር እንዳለ ግኝቱ አሳይቷል። በተጨማሪም፣ እድሮች የተለያዩ ኃይማኖት ተከታዮችን አንድ ላይ በማሰባሰብና ግንኙነቶችን በመፍጠር ረገድ ቅዳሚ መድረኮች ሆነው ተገኝተዋል።
  • የጅማ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተደራሽነቱን ለማስፋት እና ተጨማሪ የግጭት ቅድመ መከላከል እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት እና መጠናከር አለበት። ከዚህ ጎን ለጎን የመሬትንና የሕዝብ መገልገያ ቦታዎችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ግልፅ ደንቦችን ማውጣት ያስፈልጋል። በተጨማሪም የመንግሥት ባለሥልጣናት የኃይማኖት ገለልተኝነትን እና የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ፍትሐዊ የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥን የሚያረጋግጡ ሕገ መንግሥታዊ አሠራሮችን መቀየስ አለባቸው።

Find the English version of this report here.

  • Recent Publications