የሴቶች ሚና በኢትዮጵያ ክልልላዊ እና አገር አቀፍ የሰላም ሂደቶች

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሴቶች የተለያዩ የፖለቲካ፣ የጸጥታ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ተግዳሮቶች ያጋጥሟቸዋል። በሌሎች አገሮች እንደሚታየው ሁሉ፣ በኢትዮጵያ የሚከሰቱ ግጭቶች ሴቶችን ተመጣጣኝ ላልሆኑ ስቃዮች፥ ጥቃቶችና እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ያጋልጧቸዋል። ይህም የሰላምን አስፈላጊነት የሚያጎላ ሲሆን፣ የሴቶችን እና የልጃገረዶችን ደኅንነት ከማረጋገጥ ባለፈ የሴቶችን መብት ከማክበር ጋር የተያያዘ ነው። ከዚህ ጎን ለጎን የሰላም ሂደቶችን ዘላቂነት እና ህጋዊነት ለማረጋገጥ ትርጉም ያለው የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ ነው። በአሁኑ ጊዜ ግን ሴቶች በተለያዩ ደረጃዎች ሙሉ ብቃት ያላቸው ሰላም ፈጣሪዎች መሆናቸውን በተደጋጋሚ ቢያሳዩም ለሰላም መስፈን የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ እጅግ በጣም አነስተኛ ነው። ይህ ጽሑፍ የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ሂደቶችን በምሳሌነት በመጠቀም በእነዚህ ሁለት ሂደቶች ውስጥ የሴቶች መካተት እስካሁን በታዩት ውጤቶች ላይ እንዴት ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ያሳያል።

Find the English version of this briefing here.

  • Recent Publications

    የድንበሮች ውዝግቦችና ሊያስከትሉት የሚችሉት ምስቅልቅል: በምስራቅ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚታየው የወሰን ውዝግብና እና ጥንቃቄ የሚሻው የሰላም ጥረት

    በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልል ድንበር አካባቢ የሚገኙ አከራካሪ ቦታዎች ላይ አስተዳደራዊ ቁጥጥርን ለማጠናከር በሚደረገው ፉክክር የሚነሱ ግጭቶች የተዳፈኑ ቢመስሉም ጨርሰው አልጠፉም። ይህ በምስራቅ አፍሪካ ረጅሙ

    MORE »

    የከተሞች ውዝግቦች በኢትዮጵያ፡ የድሬ ዳዋ፥ ሐዋሳና ሆሳዕና ጥናቶች ጭምቅ

    በኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ያሉ ከተሞች ውስጥ የሚታዩ ውዝግቦችን ማጥናት ከመዲናይቱ በመቀጠል ያሉ ከተሞች ጉልህ በሆኑ የማኅበረ-ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጦች መሐል እንዴት እየተለዋወጡ እንደመጡ ለመረዳት ያግዛል። የኢትዮጵያ

    MORE »