Search
Close this search box.

Rift Valley Institute

Making local knowledge work

የጠረፍ አካባቢዎች የአገር በቀል የኢኮኖሚ ልማት ጥያቄዎችና የስኳር ልማት

ማጠቃለያ 

  • ብልጽግና ፓርቲ በ2010 (እ.ኤ.አ. በ2018) ወደ ሥልጣን ከመጣ ሲመጣ፣ መንግሥት ብዙ ሺህ ሄክታር የሚሸፍኑ የአገዳ እርሻዎችን ጨምሮ ስምንት የስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል ይዞታ በማዘዋወር የኢትዮጵያን የስኳር ኢንዱስትሪ ያነቃቃል የሚል ግምት ተስፋፍቷል። ይህ አመለካከት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዲግ) መራሹ መንግሥት መንግሥት-መር የልማት ስትራቴጂ ዋና አካል የሆኑት የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በተከታታይ ያስከተሉት ከዕቅድ በላይ ወጪቸች፥ የንድፍ/ዲዛይን ግድፈቶች እንዲሁም የቴክኒክ ማሻሻያዎነን ተከትሎ የመጣ ነው። 
  • በደቡብ ኦሞ ቆላማ አካባቢዎች (አሁን አዲስ የተመሠረተው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አካል) በ2003 (እ.ኤ.አ. በ2011) የተመሠረተው ኩራዝ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በመንግሥት የሚመራና በመጠኑ ወደር የለሽ ምርት የሚያመርት የግብርና ልማት እቅድ ነው። በኢህአዲግ ዘመን በርካታ ፈተናዎች ያጋጠሙት ይህ ፕሮጀክት፣ በብልጽግና ፓርቲ የስኳር ዘርፍ ማሻሻያ እና የፕራይቬታይዜሽን (ወደ ግል ይዞታ ማዛወር) መርሐ ግብር ቢደረግም ችግሮቹ ቀጥለዋል። ኩራዝ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በዘርፉ ለሚታዩት ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እና የግጭት ምንጮች መማሪያ መሆን የሚችል ዘርፍ ነው። 
  • የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገው ወጪ አስቀድሞ እንደተገመተው ከፍተኛ ቢሆንም፣ እስካሁን የፈሰሰው ከፍተኛ መጠን ያለው መዋለዕ ነዋይ ለመመለስ የማይቻል ወጪ ከመባል ያለፈ እንደሆነ መታየት አለበት። ለአካባቢው ማኅበረሰብ ያመጣው የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አለመኖር እንዲሁም በክልሉ መልክዓ ምድር ላይ የመጡ የማይቀለበሱ ለውጦችን ከግምት ውስጥ በማስገባት፥ ፕሮጀክቱን ያለ ተጨማሪ አሉታዊ ውጤቶች ማቆም አይቻልም። 
  • የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ያልተሳካ አተገባበር ተፅዕኖዎች በርካታ መልክ አላቸው። ከቀድሞው የኢሕአዴግ አመራር ጋር ቁርኝት ያላቸው ከፍተኛ ባለስልጣናትና ኮንትራክተሮች – የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን (ሜቴክ) ጨምሮ – ከዘርፉ ገለል ተደርገዋል። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን (አሁን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ቡድን) በብልጽግና ፓርቲ ሥር መሠረታዊ ማሻሻያ ተደርጎበት የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በከፊል ለግል ተጫራቾች የሚሸጥበትን ሁኔታ አመቻችቷል። 
  • መሬት ላይ ባለው እውነታ፣ ማኅበረ-ባህላዊ ለውጦች በአካባቢያዊ ለውጦች፣ ልማዳዊ የግብርና አርብቶ አደር መሬት አጠቃቀም ልማዶች እና የሠራተኞች ፍልሰት በዋናነት የአካባቢው የኑሮ ሁኔታ ላይ ጫና በማሳደር ደዳት አድርሰዋል። ይህ በርካታ ገዳቶች ይኖሩታል፤ በተለይም በፕሮጀክቱ ላይ በአካባቢ ተቃውሞ እንዲበረታ ማድረግና ማኅበራዊ ግጭትን ማባባስ ያሉ ጉዳቶቸ። ስለሆነም የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክትም ሆነ መሰል ግዙፍ ፕሮጀክቶች የረጅም ጊዜ ስኬትን እንዲያስመዘግቡ ከታሰበ ከአካባቢው ማኅበረሰቦች ጋር የደሚረጉ ምክክሮችና እና ስምምነቶች ቅድመ ሁኔታ መሆን ይኖርቸባለል። 
  • የኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የወደፊት አካሄድን በተመለከተ ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ይኖራሉ። እነሱም፣ ፕሮጀክቶችን ወደ ግል የማዛወር ጨረታ ሒደት ግልፅነትና ተጠያቂነትን ማስፈን (ውጤታማ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ጨረታ ሥርዓት መዘርጋት፣ የጥቅም መጋራት አማራጮችን ማበጀት እንዲሁም አሳታፊ የውሳኔ አሰጣጥ መዋቅሮችን መዘርጋት) አሳታፊ የሀብት አስተዳደር ሥርዓት ማበጀት (ማኅበረሰብ ተኮር ጥብቅ ፈፍራዎነን ዘማጋጀት) ለሎም የማካካሻ እና የማገገሚያ ስትራቴጂቸችን መንደፍ (ለማህበራዊ አገልግሎቶች አቅርቦት እና ለኑሮ ኪሳራ ማካካሻ ትኩረት በመስጠት) መሥራት ያስፈልጋል። 

Find the English version of this report here.

  • Recent Publications